ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ምክክር አካሄዱ

EED ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ መንግሥት ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት እና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በማሰብ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙንና ወደስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ነገሮችን ሰከን አድርጎ ማየትና ማመዛዘን እንዲሁም ለሚያጋጥሙ ችግሮቹ ትክክለኛውን መንስኤ  በአግባቡ በመለየት ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፈልግም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በበኩላቸው መሰረታዊ በሆኑና አለመግባባቶች በሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ልዩነቶችን ሊያስተናግድ የሚችልና የሀገራችንን አንድነትና ጥንካሬ ሊያሳድግ የሚችል ስርዓት እንዲኖር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ በሀገራችን ውስጥ ያሉና የነበሩ ዋና ዋና ችግሮች እና የማንግባባቸው ጉዳዮች፤ አሳሳቢ ችግሮች በሚል የሚነሱ፤ የግጭት መነሻ ምክንያቶችና የመፍትሄ ሀሳቦችን እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በዚህም የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች በሀገራዊ ምክክሩ ቢካተቱ በህዝቦች መካከል የተፈጠሩ ልዩነቶችን በማጥበብ ብሔራዊ መግባባትን ይፈጥራሉ ያሏቸውን አጀንዳዎች አቅርበዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የላቀ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!

#ስለኢትዮጵያ_ኢንተርፕራይዝ_ልማት ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com እናመሰግናለን፡፡

News