
አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ለዘርፍ ዕድገት የተመቻቹ ድጋፎችን አስተባብሮ መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ
EED (ሰኔ 12/2017 ዓ.ም)
የፌዴራልና የክልል የዘርፉ አመራርና የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ውጤታማነት ላይ ውይይትና ምክክር አድረገዋል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በመድረኩ እንደገለፁት አምራች ዘርፉ ሰፊ ድጋፍ የሚፈልግ ከመሆኑ አኳያ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲመዘገብ ለዘርፉ የተመቻቹ ድጋፎችን አስተባብሮ ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ንቅናቄ ፕሮግራም የተጀመሩ ስራዎችን በተገቢ ሁኔታ አጠናክሮ በማስቀጠል ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት እንደሚገባ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ዘርፉ ላይ ያለው አመራር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ በበኩላቸው እንደተናገሩት ዘርፉ በጥናትና ምርምር እንዲደገፍና ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች፣ መመሪያዎች ፣ የጥናትና ምርምር ስራዎች ሲዘጋጁ ኢንስቲትዩቱ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ የድጋፍ ሰነዶች ወደ ታች ወርደው እንዲተገበሩ አመራሩ ተገቢውን ግንዛቤ ይዞ መምራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በውጤታማነት ለመምራትና ለመደገፍ የቀረቡ ስትራቴጂዎችና የልማት ፕሮግራሞች፣ እንዲሁም የጥናትና ምርምርም ስራዎች ዘርፉን ለመደገፍ ምን ምቹ ዕድል አላቸው? እንዴትስ ይተገበራሉ፣ በአፈፃፀም የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዴት መፍታት ይቻላል በሚሉት ነጥቦች ላይ ሰፊ ውይይትና ምክክር ተደርጓል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com