ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀምበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተካላ ኘሮግራም ላይ ተሳተፉ ሆነዋል

EED ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከናወነ ባለው በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር፣  በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

የልማት መ/ቤቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማው ፈረደ በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ በሚገኘው የአንድ ጀምበር የ700 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ  ተሳታፊ በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለምግብነት የሚውሉና  የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚረዱ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞችን መትከላቸውን ተናግረዋል::

ልማት መ/ቤቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁም አስፈላጊውን ክትትል እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል::

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር  የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች አረንጎዴ አሻራቸውን አኑረዋል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት  #እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News