ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣  ‎የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“በ2017 እንደተቋም የተመዘገቡ ውጤቶችን በተያዘው በጀት ዓመት በተሻለ በመፈፀምና  ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣  ‎የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED (ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በዘርፉ ስራዎች፣  በተቋማዊ ብራንዲንግና ተግባቦት እንዲሁም በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም  ላይ እየተወያዩ ነው።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የውይይት መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት ከውስጥ አሰራር፣ ከተደራሽነትና ከክልሎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ባለ የስራ ግንኙነት የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገቡ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እውቅና ማግኘቱን ተናግረዋል።

የተገኘው ውጤት ዘርፉ ላይ ያለው አመራርና ሰራተኛ የጋራ በመሆኑ ውጤቱ ለቀጣይ ስራዎችም ትልቅ አቅም እንደሚሆን አስገንዝበዋል።

በ2017 በጀት ዓመት አጋማሽ የገጠር ኢንደስትራላዜሽን  ኢንሼቲቭ እንዲጀመር ተቋሙ ተልዕኮ ወስዶ መስራቱን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ ፕሮግራሙን በተመለከተ  ከክልሎችና ባለድርሻ ተቋማት ጋር በተሰራው ስራ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በዚህ ኢኒሼቲቭ ማቋቋም መቻሉንም ተናግረዋል።

ተቋሙ ባለፈው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖና በልዩ ልዩ ሀገር አቀፍና የውጭ ሀገር ባዛሮች  ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ  በገበያ ትስስርና በልምድ ልውውጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን በተያዘው በጀት ዓመት በተሻለ አቅም በመፈፀምና  ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ በተቋማዊ ብራንዲንግና ተግባቦት እና በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ላይ ሰነዶች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል::

‎#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News