ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

EED ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገለጸ፡፡

ይህ የተገለጽው የልማት መ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ባካሄዱት ውይይት ላይ ሲሆን በመድረኩም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር  ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ ከዘርፍና ከስራ ሀላፊዎች ጋር በ2018 ዓ.ም የዕቅድ ግብ ላይ  ስምምነት ፊርማ አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት  ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በሀገሪቱ የተጀመረውን ኢንዱስትሪያላይዜሽንን የማስፋፋት ተግባር ለመደገፍ በሰራቸው ጠንካራ ተቋማዊና ቅንጅታዊ ስራዎች የሚታይ ለውጥ በማምጣት በ2017 ዓ.ም ላበረከተው የላቀ አፈፃፀም ተቋሙ ተሸላሚ መሆን እንደቻለ ገልፀዋል።

ይህ ስኬት በአንድ ግዜ የመጣ ሳይሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ ተቋማዊና ሀገራዊ ሪፎርሞች፣ በትጉህ ሰራተኞች ጥረት እንዲሁም ከክልልና ባለድርሻ አካላት ጋር በተፈጠረ ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር የተገኘ  ውጤት መሆኑንም  ዶ/ር አለባቸው  አያይዘው አመላክተዋል።

በመድረኩ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ ባስተላለፉት መልዕክት  ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሽግግር በማምጣት የኢትዮጵያን ብልፅግና ዕውን ለማድረግ መንግስት ሀገር በቀል ኢኮኖሚክ ሪፎርም ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ሪፎርሙ ግቡን እንዲመታ እንደ ተቋም ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን  በማቋቋም፤ በመደገፍና በማሸጋገር የኢንዱስትሪውን መሠረት ለማስፋት የተጣለብንን ሀላፊነት በተሻለ ውጤት መፈፀም ችለናል። በቀጣይ የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል እንደሚሰራና በዚህም፣ ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተጠናከረ ቅንጅት በመስራት ለቀጣይ ስኬቶች ጉዞውን በልበ ሙሉነት እንደሚቀጥልም አስረድተዋል።

የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው የተገኘውን ስኬት መነሻ በማድረግ አምራችነትን በማስተዋወቅ፣ ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት፣ በማጠናከርና በማሸጋገር ዘርፉን የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ለማድረግ በተግባር ሰርተው ለማሳየት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

በመጨረሻም ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሠራተኛ በተገኘው ውጤት ሳይኩራራና ሳይዘናጋ በቀጣይ አሁን ከደረስንበት የላቀ ውጤት ለማምጣት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ዶ/ር አለባቸው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News