ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት አመቱን 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከዘርፍ የክልል አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ አካሄደ

EED ጥር 15 ቀን 2018 (አርባ ምንጭ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2018 በጀት አመት 6 ወራት የአበይት ተግባራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ከዘርፍ የክልል አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ አካሄደ

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በ2018 ዓ.ም በሀገራችን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች መካከል አንዱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተጀመረው ስራ አመርቂ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል።

የዘርፉ ዕቅድ የሚፈፀመው በየደረጃው ባሉ አካላት እንደሆነ የገለፁት አቶ አብዱልፈታ በትግበራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ታምርት ፕላትፎርም በመጠቀም የተገኙ ስኬቶችን በማስፋት አበረታች ውጤት እየተመዘገ እንደሆነ አመላክተዋል።

በሀገራችን በከተሞች አካባቢ ብቻ ከትመው የሚገኙትን ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በሁሉም የገጠሩ አካባቢ እንዲስፋፉ በማድረግ በየአካባቢው ያለውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታ ያለመ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሽየቲቭ ማስተግበሪያ ማኑዋል ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል።

አቶ አብዱልፈታ አክለውም ስኬቶቻችን በማስቀጠል፤ ሊሻሻሉ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር በመወያየትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ የአምራች ኢንዱስትሪውን ወደተሻለ ደረጃ ለማስቀመጥ የራሳችንን የቤት ስራ እንወስዳለን ብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News