ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

በበጀት ዓመቱ 6 ወራት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ለ90,733 ዜጎች አዳዲስ የስራ ዕድሎችን መፍጠር ተችሏል!

EED ጥር 15/ 2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2018 በጀት አመት 6 ወራት የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ እቅድ አፈፃፀምን ከክልል የዘርፍ ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች አመራሮች ጋር የግምገማ ውይይት አደረገ::

በመድረኩ የበጀት ዓመቱን ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት በተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ከላሊ ወ/ገብርኤል እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 8,493 ነባር አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከርና 2,091 አዳዲስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ለ90,733 ዜጎች አዳዲስ የስራ ዕድሎችን መፍጠር እንደተቻለ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ30,413 ብልጫ እንዳሳየ አመላክተዋል።

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 233 አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ወደ መካከለኛ ለማሸጋገር በማቀድ 498 ኢንተርፕራይዞችን የተሸጋገሩ ሲሆን በተጨማሪም 22 መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ወደ ከፍተኛ ለማሸጋገር ታቅዶ 24 ኢንተርፕራይዞችን ማሸጋገር እንደተቻለ ገልፀዋል።

ባለፉት 6 ወራት ለ4,913 ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 7,444 ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ እንደተቻለ የገለፁት አቶ ከላሊ፤ ዜጎችን በማሰልጠን ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበውን የሰለጠነ የሰዉ ኃይል ለማሻሻል በተሰራ ስራ 12,674 የሰለጠነ የሰው ሀይል ማቅረብ እንደተቻለ አብራርተዋል።

በመድረኩ ከገበያ ትስስር፤ የተኪ ምርት መጠንና ገቢን ማሳደግ ፤ የወጪ ምርት መጠንና ገቢ ማሳደግ ፤ የግብአት አቅርቦት ፤ የፋይናንስ አቅርቦት ፤ የማምረቻ ማዕከላት ልማትና አስተዳደር ፤ ኢንቨስትመንት መሳብ ፤ የማምረት አቅምና ተወዳዳሪነት ከማሳደግ አንፃር ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ አፈፃፀሞችን በዝርዝር ቀርበዋል።

በመድረኩ የክልል የዘርፉ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ም/ቢሮ ኃላፊዎችና የእቅድ ባለሙያዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የስራ አመራር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News