
ባለፉት ስድስት ወራት 118 የገጠር ወረዳዎችን ከማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ጋር ማስተዋወቅ ተችሏል
EED ጥር 15/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት አመቱ 6 ወራት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሽየቲቭ አፈፃፀምን በተመለከተ ከክልል የዘርፍ አስፈጳሚና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ::

በመድረኩ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሽየቲቭ አስተባባሪ አቶ አበበ በላይ እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት ቀደም ሲል ምንም ዓይነት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ባልነበረባቸው 118 የገጠር ወረዳዎች 243 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም የኢንዱስትሪውን መሠረት የማስፋፋት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዚህም ለ5,389 በገጠር የሚኖሩ ዜጎች ከግብርና ውጪ አዲስ የሥራ እድል ፈጥሯል ያሉት አቶ አበበ ይህ ውጤት በገጠር አካባቢዎች የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል፣ ድህነትን ለመቀነስና ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፅንሰ-ሀሳብ በአካባቢ የሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችን፣ እውቀትን፣ ችሎታዎችንና ጉልበትን በመጠቀም ለገጠር ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመፍጠርና በማስፋፋት ላይ ያተኮረ ነው።
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!