
የማብቃት ፕሮግራም የ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ
EED የካቲት 19/2018 ዓ.ም (አዳማ)

አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ማዕከል በማድረግ ለወጣቶች በተለይም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተተገበረ የሚገኘው የማብቃት ፕሮግራም የበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ::
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደተናገሩት መድረኩ የተዘጋጀው የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ለመወያየትና የቀጣይ ስራዎች ላይ መግባባት በመፍጠርና የጋራ ተልእኮ በመውሰድ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነትን ማሳደግ ነው፡፡

የፔትኮ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ምህረት ተክለማርያም በበኩላቸው ማብቃት ፕሮግራም በወጣቶች በተለይም በሴቶች የሚመሩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋምና በማጠናከር ተጨማሪ የስራ እድል እንዲፈጥሩ ለማድረግ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የማብቃት ፕሮግራም የበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የማብቃት ፕሮግራም ፔትኮ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ካዌ በጋራ በመሆን እየተተገበረ ያለና 6,355 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ በማድረግ ለ241,696 ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠርን ዒላማ አድርጎ የሚሰራ ነው፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት