ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከአማራ ክልል የአነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ

EED የካቲት 21/2018 ዓ.ም (ቢሾፍቱ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች ጋር የአነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ልማትን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ውይይት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በመድረኩ እንደተናገሩት የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ለስራ እድል ፈጠራና ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የአማራ ክልል የአስፈጻሚ አካላትን በአዲስ መልክ ሲያደራጅ የአነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ልማት ስራን በስራና ክህሎት ቢሮ እንዲመራ መደረጉን አስታውሰው የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ልማት መ/ቤቱ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫዎች በተመለከተ ግንዛቤና የጋራ መግባባት ለመፍጠር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ አነስተኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከርና አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር ከድህነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት መደገፍ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የልማት መ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር መወሰኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 526/2015 እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለጻ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም የበጀት ዓመቱ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም፣ የቀጣይ ወራት እቅድና የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሺየቲቭ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷባቸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News