ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስራዎች አፈጻጸምና የቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል

EED ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሠራተኞች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስራዎች አፈጻጸምና የድህረ ምርጫ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የውይይት መድረኩን የከፈቱት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ 7ኛው ጠቅላላዊ ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸው ለዚህም የህብረተሰቡ ሚና የላቀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በምርጫ ሂደት ዉስጥ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት መመስገን አለባቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ መድረኩ የተዘጋጀው ምርጫው በሰላም በመጠናቀቁ ለማመስገንና የምርጫው ውጤት እስከሚገለጽና አዲስ መንግስት እስኪመሰረት ድረስ እንደዜጋና እንደኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ሠራተኛ ምን ይጠበቅብናል የሚለውን ለመወያየት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በመድረኩ ‹‹ከምርጫ ድል ማግስት፣ ጠንካራ መንግስት›› በሚል መሪ ሃሳብ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስራዎች አፈጻጸምና የድህረ ምርጫ ስራዎች ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ አቅርበዋል፡፡ 

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

#ለተጨማሪ_መረጃ_የማህበራዊ_ሚዲያ_ገጾቻችንን ይጎብኙ!

‌‎https://linktr.ee/Ethiopianenterprisedevelopment

News