ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮች በቂሊንጦ ልዮ የኢኮኖሚ ዞን አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

EED ነሐሴ 8/2018 ዓ.ም

​የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቂሊንጦ ልዮ የኢኮኖሚ ዞን በመገኘት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አከናወኑ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የልማት መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረትን መጠበቅና ምቹ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የተቋሙ እንቅስቃሴ ችግኞችን በመትከል ብቻ የሚገደብ ሳይሆን፣ ተክሎቹ አድገውና ፀድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲበቁ ዘላቂ ክትትልና እንክብካቤ ማድረግን ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል።

ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ መርሃ-ግብር የተተከሉ ችግኞች ያሉበት ደረጃ  መጎብኘቱንና አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንም አረጋግጠዋል።

​የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋምና በማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የማስቻል ዋና ተልዕኮ እንዳለው የጠቆሙት ዶ/ር አለባቸው፤ ከዚሁ ዋና ሥራ ጎን ለጎን ለአካባቢ ጥበቃና ለአገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ጥሪ ምላሽ መስጠት የተቋሙ የማህበራዊ ኃላፊነት አካል መሆኑን አስረድተዋል።

​በተጨማሪም እንደ ተቋም ከመደበኛ ስራዎች ጎን ለጎን የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እንዲከናወኑ ሁሉም አመራርና ባለሙያ ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

​ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የደን ሽፋኗን ለማሳደግ እያካሄደች ባለው ሀገራዊ ንቅናቄ መሠረት፣ እንደ ቂሊንጦ ባሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ የሚከናወኑ የችግኝ ተከላዎች የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስና አረንጓዴ የኢንዱስትሪ ምህዳር ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

#አረንጓዴ_አሻራ

​ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News