
በ2018 በጀት ዓመት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች 270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል!
ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
EED መስከረም 9/2019 ዓ.ም (አዳማ)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት አዲስ በተቋቋሙና በተጠናከሩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች 270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አስታወቀ::
ይህ የተገለጸው ከመላው ኢትዮጵያ ለተወጣጡ 160 ለሚሆኑ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት በተጀመረበት ወቀት ነው።

የልማት መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ተቋሙ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 526/2015 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ ሆነው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር፣ በተኪ ምርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በኤክስፖርት እድገት ላይ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 4 ሺህ 233 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች መቋቋማቸውንና በዚህም ለ270,546 ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል::

ከዚህም በተጨማሪ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሰራው ስራ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን መተካት መቻሉንና ወደውጭ በተላኩ ምርቶች 36 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዶላር መገኘቱን ተናግረዋል::
ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የዘርፉን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚሰጡ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን፣ የእድገት ሽግግር፣ የቴክኖሎጂ ልማት፣ የጥራት አስተዳደርና የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ስራዎችና ድጋፎች የተሳለጡና ወጥ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ በየአካባቢያቸው ለሚገኙ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች አቅም የሚገነባና ውጤታማ ድጋፍ እንዲሰጡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አደራ ብለዋል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment