ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እና ባለሙያዎችን ለመደገፍ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ

​EED መስከረም 5/2019 ዓ.ም

​የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በአማራ ክልል 5 ከተሞች የሚገኙና በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እና ባለሙያዎችን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

​መድረኩን የከፈቱት የልማት መ/ቤቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማው ፈረደ እንደተናገሩት፣ ፕሮግራሙ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እና ዘርፉን የሚደግፉ ባለሙያዎች በስነ-ልቦና እንዲዘጋጁ ከመደገፉም በላይ በዘላቂነት ወደ ሙሉ ምርትና አገልግሎት እንዲመለሱ የሚያስችል  ስራዎችን ያካተተ ነው።

ከዚህ በፊት በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ወደነበሩበት የስራ መንፈስ እንዲመለሱና እንዲነቃቁ የስነ ልቦና ማነቃቂያ መርሃ ግብር መካሄዱን አውስተዋል::

​ከጀርመን አለም አቀፍ የልማት ድርጅት (GIZ) እና አጋር ተቋማት በተገኘው ድጋፍ የሚተገበረው ይህ  የአቅም ግንባታ ፕሮግራም በደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር እና ደብረ ብርሃን የሚገኙ 75 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም 25 ባለሙያዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

​

በዚህ ይፋዊ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ ከአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ፣ ከስራና ክህሎት ቢሮ እና ፕሮግራሙ ከሚተገበርባቸው 5 ከተሞች የመጡ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!

​ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News