ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

“የኛ ምርት፣ ለእኛ” የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር!

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከጆርካ ኤቨንትስ ጋር በመተባበር ከታህሳስ 18-27/2017ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍልውሃ አካባቢ በሚገኘው ፊንፊኔ ሆቴል አጠገብ የሚካሄድ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ባዛር አዘጋጅቷል፡፡

“የኛ ምርት፣ ለእኛ” የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር! በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ #ሀገር_አቀፍ ባዛር በአልባሳትና የቆዳ ውጤቶች፣ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች፣ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ በኬሜካልና ኬሜካል ውጤቶች፣ በጌጣጌጥና ማዕድን ፣ በኮንስትራሽን ግብዓት የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ይሳተፋሉ፡፡

ባዛሩ ለገበያ ተመራጭ በሆነ ቦታ የሚካሄድ በመሆኑ ጥሩ ሽያጭና የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ዘላቂ ደንበኞችን ለማፍራት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

ስለሆነም አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ፈጥናችሁ በመመዝገብ የባዛሩ ተሳታፊዎች በመሆን ግብይት አከናውኑ፤ ምርቶቻችሁን አስተዋውቁ፤

ባዛሩ ከታህሳስ 18-27/2017 ዓ.ም ይካሄዳል፤

“የኛ ምርት፣ ለእኛ” የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር!

News