
የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የገበያ ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ተዘጋጀ
EED፡ ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘጋጀው የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደተናገሩት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተዘጋጀው የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት የገበያ ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው::

ለዘርፉ ሰፊ የሀገር ውስጥና የውጭ ሃገር የገበያ መዳረሻዎችን የሚፈጥር ዘመን አመጣሽ መተግበሪያ እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር አለባቸው የኤሌክትሮኒክስ ግብይቱ ደህንነቱ የተጠበቀና ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል የግብይት ስርዓት መፍጠር ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማብቃት ጥራት ያለው ምርት በኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓቱ ላይ ማቅረብ እንዲችሉ ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ መስጠት እንደሚቀጥልና ከተለያዮ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አመላክተዋል።

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በመተባበር የተዘጋጀውን የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ያዘጋጀው ሲ ኤስ ኤም አፍሪኮም የተባለ አማካሪ ድርጅት ሲሆን የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ምርቶችን ለተጠቃሚዎች የሚያደርስ ይሆናል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
ተጨማሪ መረጃ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com