
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የወረቀት አልባ አሰራር ስርዓትን (Paperless Office) ተግባራዊ ሊያደርግ ነው
EED ሚያዝያ 7/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የወረቀት አልባ አሰራር ስርዓትን (Paperless Office) ተግባራዊ ለማድረግ ለስራ ለተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በስልጠናው መድረክ የተገኙት የልማት መስሪያ ቤቱ ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ከላሊ ወ/ገብርኤል እንደገለፁት እንደ ሀገር እየተሰራ ከሚገኘው ሪፎርም አንዱ አሰራሮችን ዲጂታል ማድረግ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የወረቀት አልባ የአሰራር ስርዓትን ለመተግበር የተለያዩ ተግባራት ሲያከናውኑ እንደቆዮ የገለፁት አቶ ከላሊ የመንግስት ሰነድና ደብዳቤ አስተዳደር ስርዓት (GDOP) ዲጂታል ለማድረግ እንቅስቃሴዎችን እንደጀመሩ አመላክተዋል፡፡ የአሰራር ስርዓቱን ወደተግባር ለማስገባት ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልጸዋል::
ተግባራዊ የሚደረጉት የአሰራር ስርዓቶች የሰነድ/ደብዳቤ አስተዳደር ስርዓት /DMS/፣ የጉብኝት አስተዳደር ስርዓት (VMS) እና የትራንስፖርት ስምሪት አስተዳደር ስርዓት ናቸው፡፡

የመንግስት ሰነድና ደብዳቤ አስተዳደር ዲጂታል (GDOP) ስርዓት የወረቀት ንክኪን የሚያስቀር ከመሆኑም ባለፈ በርካታ ተገልጋዮችን በአጭር ጊዜ ማስተናገድ ከማስቻሉም ባሻገር ቀልጣፋ እና ግልጽነትን የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችልም አቶ ከላሊ አያይዘው ገልፀዋል።

ከደህንነት አኳያ ዲጂታል ፊርማ ያለው በመሆኑ የይዘት ለውጥ የተደረገበትን ደብዳቤ በቀላሉ መለየት የሚችል በመሆኑ ከስጋት ነፃ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡
ሲስተሙን ወደ ተግባር ለማስገባት ለተቋሙ መሪ ስራ አሰፈፃሚዎች፣ ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዴስክ ኃላፊዎች፣ ሹፌሮች እንዲሁም ለፀሃፊዎችና ለመዝገብ ቤት ባለሙያዎች የተግባር ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!