ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ

EED ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት  ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደተናገሩት የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሠረት የመጣልና የማስፋት ስራን በአሰራር በማስደገፍ ለመምራት የሚያስችል ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስትራቴጂ ማዘጋጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ይህ ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው የውይይት መድረክ ከዚህ ቀደም ከልማት መስሪያ ቤቱ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎች በረቂቅ ስትራቴጂው ላይ የሰጧቸው የማሻሻያ አስተያየቶች በሰነዱ ላይ መካተታቸውን ለማየትና ተጨማሪ አስተያየት ለመስጠት መዘጋጀቱን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሰነዱ የአምራች ኢንተርፕራይዞችን ብቃትና ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ የአመራረት ሂደት ጥራት ያለው የአመራረት ስርአትን የሚያመላክት እንዲሁም የስራ ቦታና የአካባቢ ደህንነት በማረጋገጥ ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር የሚቻልበትን መንገድ በግልፅ በሚያሳይ መንገድ መዘጋጀት እንደሚገባው በመድረኩ ተመላክቷል። 

በመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በዋናነት ሰነዱ ከወቅቱ የአሰራር ስርዓት ጋር የተጣጣመ፣ ችግር ፈቺ እና አጠቃላይ የሃገሪቱን ቀጣይ የእድገት አቅጣጫ ያማከለ እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀት እንደሚገባው ተጠቅሷል።

የስትራቴጂ ዝግጅቱ በኮንሱል አማካሪ ድርጅት  እና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ በጋራ እየተሰራ ሲሆን አማካሪ ድርጅቲ የተሰጡትን አስተያየቶች በማካተት በፍጥነት አጠናቆ እንዲያቀርብም ጥሪ ቀርቧል::

በመድረኩ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት፣ ከፔትኮ ኢትዮጵያ፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት፣ ከስራና ክህሎት ሚንስቴርና ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዮትና ከአማካሪ ድርጅቱ የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com እናመሰግናለን::

News