ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ልዩ የማበረታቻ ድጋፍ ለማስቀጠል ያለመ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ተፈረመ

EED ሕዳር 19/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ በቀላሉ እንዲልኩና ጥሬ ዕቃ፣ ማሽነሪና አክሰሰሪ እንዲያስገቡ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በፊርማ ስነ-ሥርአቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት፤ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት ሊያሳድጉ የሚያስችሉ ማበረታቻዎችን መስጠት የሚያስችል ቅንጅት ለመፍጠር ሁለቱ ተቋማት ተደጋግፈዉ በመስራት የተናጠል እና የጋራ ኃላፊነትና ተግባራቸዉን ውጤታማ በሆነ ሁኔታ መወጣት የሚስችላቸው መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ቀልጣፋና ቅድሚያ የሚሰጥ አገልግሎት መስጠት፤ የገቢና ወጪ መረጃ በፍጥነት ማቅረብ፤ ለኤግዚቢሽንና ናሙና ምርት ፈጣን አገልግሎት መስጠት፤ ወርሃዊ የኢንተርፕራይዝ ኤክስፖርት መረጃ ለልማት መስሪያ ቤቱ መላክ እንዲሁም የማበረታቻ ፓኬጆች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ መስጠትና መሰል አገልግሎቶችን በላቀ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ሁለቱም ወገኖች በመግባቢያ ሰነዱ ውስጥ በተናጠልና በጋራ ለመስራት የተስማሙበትን ተግባሮች በመስራት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን የተወዳዳሪነት አቅም ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት 

#የኢትዮጵያ_ኢንተርፕራይዝ_ልማት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ቲክ_ቶክ:  https://www.tiktok.com/@et.enterprisedevelopment

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News