ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በሚቀርበው የንግድ ስራ ልማት አገልግሎት /BDS/ የትግበራ ሂደትና ውጤታማነት ተገመገመ

EED ጥር 7/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በኮንሱል /CONSOL/ አማካሪ ድርጅት አማካኝነት ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች እየተሰጠ ያለው የንግድ ስራ ልማት አገልግሎት /BDS/ የትግበራ ሂደትና ውጤታማነት ተገመገመ፡፡

በመድረኩ ከገበያ ልማት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተከታታይ ስልጠናዎች ለአምራች ኢንተርፕራይዞች መሰጠቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቶችን በተቀመጠለት የግዜ ሰሌዳ አለማጠናቀቅ፤ አዳዲስ አለም አቀፍ ዕውቀቶችን በማምጣት አለማሸጋገር እንዲሁም የተለዩና መተግበር የሚችሉ የስልጠና ማኑዋሎችን ከማዘጋጀት ረገድ ሊሻሻሉ የሚገቡ ስራዎች እንዳሉ ተጠቅሷል፡፡

በቀጣይ አዳዲስ አለም አቀፍ እውቀቶችንና ዲጂታል ማርኬቲንግ ከማስፋት አንፃር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በበጀት አመቱ በፕሮጀክቱ አማካኝነት 400 የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የንግድ ልማት አገልግሎት (BDS) ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው::

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

News