ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ድጋፍ መስጠት እንዲቻል  ለዘርፉ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

EED ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም (አዳማ)

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ኮንሱል ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ለሚደግፉ የፌደራልና የክልል አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ባለሙያዎች ላለፉት 11 ቀናት ሲሰጥ የነበረው  የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የማኑፋክቸሪንግ  ኢንተርፕራይዞች እድገት ለማፋጠን በዕውቀት ላይ የተመሰረተ፣ ቅንጅታዊና ተግባራዊ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚህም አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በማጣቀስ፣ የተቀናጀ ድጋፍፀማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በኢኮኖሚው ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ ያስችላል ብለዋል።

በተጨማሪም እንደዚህ ያሉ ሥልጠናዎች የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት የኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት እና ዘላቂነት ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

ሰልጣኞች በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደም የባለድርሻ አካላት ሚና በስብሰባዎች ብቻ የተገደበ እንደነበር ገልፀው፣ ይህ ሥልጠና በዘርፉ ውስጥ ያለውን የድጋፍ አገልግሎት አስፈላጊነትና አፈፃፀም በግልፅ እንዲገነዘቡ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል።

በተለይ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስ፣ በገበያ ተደራሽነትና በአመራር ጉዳዮች ለመደገፍ የሚያስፈልጉ ተግባራዊ ክህሎቶችን መማራቸውን አመልክተዋል።

በቀጣይም ተቋሙ እና ባለድርሻ አካላት የአምራች ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍ ለማጠናከር በተቀናጀ መልኩ እንደሚሰራ ተገልፆ ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

የንግድ ስራ እቅድ አዘገጃጀት፣ እሴት ሰንሰለት ልማት፣ ፋይናንስ አቅርቦት አጋርነት፣ ንግድ ልማት ክህሎት እና ስትራቴጅካዊ አጋርነት እና የባለድርሻ  አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ዙርያ ስልጠና የተሰጠባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው::

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News