ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ የሚደረግ ርብርብ ለሀገር እንደሚከፈል መስዋዕትነት ይቆጠራል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED: መስከረም 29/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያዘጋጀውና የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች የተገኙበት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ ዕቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ እቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የልማት መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደገለፁት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለሀገራዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን በማመላከት ያሉትን ውስን ሀብቶች መለየትና የጎደለውን ለማሟላት ያለዕረፍት መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ይህም የሀብት እጥረትን በብልህነት እና ቀጣይነት ባለው ጥረት ለመፍታት የሚያስችል አቀራረብ እንደሚያስፈልግ ያመላከቱት ዶ/ር አለባቸው ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ የሚደረግ ርብርብ ለሀገር እንደሚከፈል መስዋአዕትነት እንደሚቆጠር በማመላከት አስፈፃሚ አካላት በቀጣይ ለዘርፉ ዕድገት ማነቆ የሚሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አዳዲስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ ፕሮግራም ከመፍጠር ባሻገር የተመዘገቡ መልካም ጅማሮዎች ወደ ኋላ እንዳይቀለበሱ በመከታተልና በመደገፍ ማስቀጠል እንደሚገባ በማመላከትም የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

እንዲህ አይነት መድረኮች የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር ሲሆን፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች ተሳትፎ የእቅዱን ትግበራ ለማሳካት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢንሺየቲቩ አስተባባሪዎችና የእቅድ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት 

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenter

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News