
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአምራች ኢንተርፕራይዞች ለ201 ሺህ 988 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጠረ
EED ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለ201 ሺህ 988 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡፡
የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንዳሉት የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም አጠቃቀም ለማሳደግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ከአስፈጻሚና ባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት ተሰርቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ለኢንተርፕራይዞች የማምረቻ ቦታ፣ የፋይናንስና የግብዓት አቅርቦትን ከማሳካት ባለፈ የተለያዩ የተግባር ተኮር ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይም አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲቋቋሙና ወጪና ተኪ ምርቶች ላይ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል ተሰርቷል፡፡
በተጠናቀቅ በጀት ዓመት 4 ሺህ 285 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም መቻሉን አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል 12 ሺህ 481 ነባር ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር ታቅዶ 15 ሺህ 4687 አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር ተችሏል ነው ያሉት፡፡
አዲስ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋምና ነባሮችን በማጠናከርም ለ201 ሺህ 988 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ በተጀመረው የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሼቲቭ 381 የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በገጠር ወረዳዎች እንዲቋቋሙ የተደረገ ሲሆን ለ2,761 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
ተጨማሪ መረጃ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment