ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

“በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የተሰሩና የመጡ ለውጦች የሚበረታቱና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ የሚሆኑ ናቸው!”

ከተለያዮ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ልዑካን ቡድን አባላት

EED ነሐሴ 26/2017 ዓ.ም

በሀገራችን በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የተሰሩና የመጡ ለውጦችን በተመለከተ ከተለያዮ የአፍሪካ ሀገራት ለመጡ የልዑካን ቡድን ገለፃ ተደረገ::

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በመድረኩ እንደተናገሩት መንግስት ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በሰጠው ትኩረት በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል::

ልማት መ/ቤቱም አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከአስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል::

በገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሼቲቭ አማካኝነት አዳዲስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በገጠር ወረዳዎች  እንዲቋቁሙ መደረጉን የገለጽት አቶ አብዱልፈታ በ2018 በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል::

አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በዓለም አቀፍ ገበያ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የምርት ጥራት ደረጃ  የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ በርካታ ስራዎች መሰራቱን ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል::

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የህዝብ ግንኙነት ኮሙኑኬሽን ተ/ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሮቤል አህመድ ልማት መ/ቤቱ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንና በዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን በተመለከተ ከሌሴቶና ቦትስዋና ለመጣው የልዑክ ቡድን አባላት ገለጻ አድርገዋል::

የልዑክ ቡድኑ አባላት ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለጻ አመስግነው በኢትዮጵያ በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የተሰሩና የመጡ ለውጦች የሚበረታቱና ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ የሚሆኑ መሆናቸውን ገልፀዋል::

‎#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

‎ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News