ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ ጳውሎስ በርጋ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

“በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ታቅደው የሚሰሩ ስራዎች እድገት እያሳዩ ነው!”

አቶ ጳውሎስ በርጋ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

EED ጥር 15/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከክልል የዘርፍ አመራሮች ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ የ2018 በጀት አመት 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል::

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ በመድረኩ እንደገለፁት በበጀት አመቱ ስድስት ወራት ታቅደው የተሰሩ ስራዎች እድገት እያሳዩ መምጣታቸውን ገልፀው እውነተኛ ብልፅግና ማሳካት የሚቻለው ሁሉንም ዜጋ ተጠቃሚ ያደረገ ስራ ሲሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

በበጀት አመቱ ከመስሪያ ቦታ አቅርቦት፤ የሰለጠነ የሰው ሀይል አቅርቦት፤ ከግብአት አቅርቦትና ትስስር፤ የቅንጅት ስራዎችን አጠናክሮ ከማስቀጠል አንፃር፤ የተደራጀ የማኑፋክቸሪንግ መረጃ (ERP) ከማደራጀት፤ ሊዝ ፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ የተጀመሩ አበረታች ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጣ ያግዛል ተብሎ የሚጠበቀው የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ በመሆኑ የክልል የዘርፍ አመራሮች ክፍተትን መሠረት ያደረገ ድጋፍ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ሊሰጡ እንደሚገባ አቶ ጳውሎስ አመላክተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News