ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

በኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ዙርያ ለአምራች ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች ስልጠና ተሰጠ

EED ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘጋጀው የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ዙርያ ለኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች  በአዲስ አበባ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በመተባበር  በሲ ኤስ ኤም አፍሪኮም አማካሪ ድርጅት አማካኝነት የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ተዘጋጅቷል::

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓቱ የኢንተርፕራይዞችን የሀገር ውስጥና የውጭ የገበያ ተጠቃሚነት ለማስፋት ወሳኝ  እንደሆነ አብራርተዋል። 

ከስልጠናው በኃላ አምራች ኢንተርፕራይዞቹ ፕላትፎርሙን በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስበው ልማት መ/ቤቱ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በመጀመሪያው ዙር ስልጠና 50 የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት  #እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News