አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

“በክልሎች መካከል ተመጣጣኝ እድገት ማምጣት ከተፈለገ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን መተገበር ግድ ነው!”
አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር
EED መስከረም 28/2018 ዓ.ም
በክልሎች መካከል ተመጣጣኝ እድገት ማምጣት ከተፈለገ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን መተገበር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ገለፁ::
ይህን የገለፁት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሺየቲቭ በተመለከተ ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው።

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለብዙ ዘመናት ከገጠሩ ማህበረሰብ በርካሽ ዋጋ የሚወጣው ጥሬ ዕቃ ግብአት እዛው በገጠር ወረዳዎች ላይ እሴት ተጨምሮበት በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ የሚቀርብበት አጋጣሚ የሚፈጥር ፕሮግራም ነው ያሉት አቶ አብዱልፈታ ፕሮግራሙን ለማስፈፀም የተለያዩ ችግሮች እያጋጠሙን ቢሆንም ያለንን ሀብት ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስገባት መስራት አለብን ብለዋል።

ከፋይናንስ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ጥያቄዎች የዞኖችና የክልሎች አመራሮች በክልላቸው ለሚገኙ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ዋስትና በመስጠት ብድር እንዲያገኙ ማድረግ አለባቸው ያሉት አቶ አብዱልፈታ የፋይናንስ ችግር አለማቀፍ ችግር በመሆኑ ፈጠራ የታከለበት መፍትሄ መውሰድ ይገባል ብለዋል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዘላቂ እድገትን የሚያመጣ ዘርፍ እንደመሆኑ መጠን በችግሮች መካከልም ብንሆንም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የፈጠረውን ቅንጅታዊ አሰራር ስርአትና መዋቅር በመጠቀም ማነቆዎችን በመፍታት በ2018 በጀት ዓመት ቀሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የገጠር ወረዳዎች ቢያንስ አንድ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ማቋቋም እንደ ግዴታ ሊወሰድ እንደሚገባ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com