ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

በድሬዳዋ ሲካሄድ የነበረው የልምድ ልውውጥና የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

EED  ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም (ድሬዳዋ)

አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ማዕከል በማድረግ ለወጣቶች በተለይም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተተገበረ የሚገኘው የማብቃት ፕሮግራምን በተመለከተ በድሬዳዋ ሲካሄድ የተበረው የልምድ ልውውጥና የምክክር መድረክ ተጠናቋል::

የማብቃት ፕሮግራም ፔትኮ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፤ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ካዌ በጋራ በመሆን እየተተገበረ ያለና 6,355 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ በማድረግ ለ241,696 ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠርን ዒላማ አድርጎ የተነሳ ፕሮግራም ነው፡፡

በመድረኩ የማብቃት ፕሮግራም የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል::

በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙና ውጤታማ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ጉብኝት፣ የድሬ ዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ ተሞክሮ ቀርቦል:፡

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደተናገሩት ለፕሮግራሙ ውጤታማነት የአስፈጻሚና ባለድርሻ ተቋማት ሚና የላቀ በመሆኑ በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጉብኝቱና ልምድ ልውውጥ መድረኩ ከድሬዳዋ የተገኘውን ተሞክሮ እንደአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በመውሰድ እንዲተገብሩም ጠይቀዋል::

የድሬዳዋ ዩንቨርስቲና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለመደገፍና ለመምራት እያደረጉ ያሉት ስራ የሚበረታታ መሆኑን የጠቋሙት ዋና ዳይሬክተሩ ሌሎች ዮንቨርስቲና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችም ቀረብ ብለው ከዘርፉ ጋር መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል::

በምክክርና የልምድ ልውውጥ መድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ የፔትኮ ኢትዮጵያና ካዌ የስራ ኃላፊዎች፣ፕሮግራሙ ከሚተገበርባቸው ክልሎች፣ ዞኖችና ከተሞች የመጡ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት 

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News