ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ  አብዱልፈታ የሱፍ ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

“አመራሩ በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም  ግንዛቤ በመፍጠር ኢንዱስትሪዎች በገጠር እንዲስፋፉ በትኩረት መስራት አለበት!”

አቶ  አብዱልፈታ የሱፍ ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

‎EED (ሰኔ 11/2017 ዓ.ም)

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ውጤታማነት ማሳደግ በሚያስችሉ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ ልዩ ልዩ ስትራቴጂዎችና የልማት ፕሮግራሞች ላይ የፌዴራልና የክልል የዘርፉ አመራርና የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ  አካላት ተወያይተዋል።

በውይይት መድረኩ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራምን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በገለፃቸው አምራች ኢንዱስትሪው ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ የድርሻውን እንዲወጣ በገጠር ያለን ሃብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አስረድተዋል።

የንቅናቄ ፕሮገራሙ በገጠር ያለን ሃብት እሴት በመጨመር ኢንዱስትሪን ማስፋፋት፣ሰፊ የስራ ዕድልና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን መፍጠር እንዲሁም በገጠር የሚኖረውን ማህበረሰብ ኑሮ ማሻሻል የሚያስችል መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከዚህ አኳያም አመራሩ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም እንዲተገበር  ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት አቶ አብዱልፈታ አመላክተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News