አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር
አምራች ዘርፉን ለሚደግፉ የፌዴራልና የክልል ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው::

“አምራች ዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን መፍጠር ያስፈልጋል!”
አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር
አምራች ዘርፉን ለሚደግፉ የፌዴራልና የክልል ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው::
EED ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም (አዳማ)
በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ኮንሱል ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር አምራች ዘርፉን ለሚደግፉ የፌዴራልና የክልል ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው::

የአቅም ግንባታ ስልጠናውን የከፈቱት የልማት መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደተናገሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ እንዲኖረን ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ ባለሙያዎች መፍጠር ያስፈልጋል::
በአምራች ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችሉና በጥናት የተለዮ ሰነዶች መዘጋጀታቸውን የገለፁት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ስልጠናው የባለሙያዎችን ክፍተትና ፍላጎት መሰረት ያደረገ በመሆኑ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል::
ለአምራች ዘርፉ የተመቻቹ እድሎችን ወደተግባር በመለወጥና በመደገፍ ኢንተርፕራይዞችን ማብቃትና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መስራት እንደሚጠይቅም አቶ ጳውሎስ ገልፀዋል::

የንግድ ስራ እቅድ አዘገጃጀት፣ እሴት ሰንሰለት ልማት፣ ፋይናንስ አቅርቦት አጋርነት፣ ንግድ ልማት ክህሎት እና ስትራቴጅካዊ አጋርነት እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ዙርያ ስልጠና የሚሰጥባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው::
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment