ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣  የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እየዘረጋን ነው!

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣  የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

ሚያዚያ 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ታምርት 2017 ኤክስፖ በተለያዩ ሁነቶች ቀጥሏል። በሦስተኛ ቀን ውሎው አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በማብቃት፣ ወደ ዕድገት፣ ተወዳዳሪነት እና ሽግግር ማፋጠን በሚል ርዕሰ ጉዳይ የፖናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት  የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደገለፁት በሀገራችን ያለው በከተሞች ላይ ብቻ የተወሰነ የኢንዱስትሪያላይዜሽን ልምምድን በመቀየር ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሁሉም የገጠር ወረዳ ድረስ ለማስፋፋት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚፈጥር የግንዛቤ ማስጨበጫ በስፋት በመስጠት የዘርፉን መሠረት የማስፋት ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።

በተለይም በአለፉት 3 የለውጥ አመታት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በፈጠረው መዋቅር በመጠቀም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የስራ ማስኬጃ ብድር፣ የመስሪያ ቦታ፣ የመሠረተ ልማት እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስጠት ሰፊ ለውጥ ማምጣት ተችሏል።

በተጨማሪም አምራች ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑና ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ፣ ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሸጋገሩ የአሰራር ስርዓት እየዘረጋን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የአምራች ዘርፉ በዘላቂነት ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባታቸውን አብራርተዋል።

በዚህ ሁሉ ሂደት አምራች ኢንተርፕራይዞች ዘመኑን የዋጁ ማሽነሪዎች፣ ቀጣይነት ያለው የንግድ ልማት አገልግሎት እንዲሁም የስራ  ማስኬጃ ብድር እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ዶ/ር አለባቸው በመንግስት የተዘረጋው የሊዝ ፋይናንስ ስርዓት ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ዕድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የፓናል ውይይቱ በዋናነት በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ኦፕሬሽን፣ ምርታማነት እና ፈጠራ የሚያሳድጉ ስትራቴጂዎችን፣  ዋና ዋና ተግዳሮቶች የሚፈቱበትን አቅጣጫዎች፣ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪላይዜሽን ጉዞ ያለውን ሚና ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

News