ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አዳዲስ ህጎችና የአሰራር ስርዓቶችን ከተልዕኮ አኳያ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

EED ጳጉሜ 04/2017 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች ‎በፕሮግራም በጀት ዝግጅትና በግዥ አፈጻጸም መመሪያ በተመለከተ ስልጠና ተሰጠ::

‎በመድረኩ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከመንግስት ግዥና ንብረት  ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች በፕሮግራም በጀት ምንነት፣ አዘገጃጀትና አተገባበር እንዲሁም የፌዴራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም መመሪያን በተመለከተ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

የመንግስት የልማት ግቦችን ለማስፈፀም  ከእቅድ ጋር የተናበበ በጀት መመደብና ስራዎችን በተቀመጠው በጀት መፈፀም እንደሚገባ አፈፃፀሙንም መከታተልና መገምገም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ባለ በጀት መ/ቤቶች ግዥን ሲያከናውኑ የግዥ አፈፃፀም መመሪያን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት የተብራራ ሲሆን በግዥ ሂደት የሚከናወኑ ተግባራትና ልዩ አስተያየት የሚሰጡባቸው ጉዳዮች ምን ምን  ናቸው፣ በግዥ ሂደት የተቋማት ኃላፊዎች ሚና ምን ይመስላል በሚሉ ሀሳቦች ላይ ግንዛቤ ተወስዷል።

የልማት መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ አዳዲስ ህጎችና የአሰራር ስርዓቶች ከተሰጠ ተልዕኮ አኳያ ስራ ላይ ማዋል እንዲያስችልና አመራርና ሰራተኛው በበጀት አመዳደብና በግዥ አሰራር ላይ የተሻለ ግንዛቤ ይዘው ውጤታማ ስራ ማከናወን እንዲችሉ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል::

በተለይም የግዥ መመሪያው የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ኢንተርፕራይዞች ጥራት ያላቸውና ተኪ ምርቶችን እንዲያመርቱ በአግባቡ መደገፍ እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ተገልጿል።

የስልጠናው ተሳታፊ ሰራተኞች‎ በበኩላቸው በበጀት ዝግጅትና ግዥ አፈጻጸም መመሪያው  ላይ የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው በእቅድ የተያዙ ስራዎችን በተቀመጠው በጀትና ጊዜ በማከናወን ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ከመድረኩ መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት 

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News