ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

‹‹ኢንተርፕራይዞች የሚሰጧቸውን ሳይንሳዊ ስልጠናዎች በአግባቡ በመተግበርና የውስጥ አሰራራቸውን በማዘመን የምርቶቻቸውን ጥራት ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል!››

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ኮንሱል ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ለ6 ቀናት ሲሰጥ የቆየውና የምርት ጥራትን ማዘመን የሚያስችሉ ርዕሶች የተካተቱበት ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽ የሰጡት የልማት መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ ከውጭ ይገቡ የነበሩ ማሽኖች በሃገር ውስጥ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ደረጃ መመረት መጀመራቸው የሚበረታታና በሰፊው መቀጠል ያለበት መሆኑን ተናግረው በዚያው ልክ ኢንተርፕራይዞች የሚታዩባቸውን ልማዳዊ የውስጥ አሰራር ክፍተቶች በሚገባ በመለየትና ከስልጠና የሚያገኙትን ሳይንሳዊ ዕውቀት ተግባር ላይ በማዋል በሚፈለገው ብዛትና የጥራት ደረጃ አምርቶ ማቅረብ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የልማት መስሪያ ቤቱ በተከታታይ በተለያዩ ርዕሶች እየሰጣቸው ያሉ ስልጠናዎች በከፍተኛ ደረጃ እንደጠቀማቸው ገልጸው ይህም ለኢንተርፕራይዞች ለውጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ከብረታብረትና እንጨት እና ከአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፎች ተውጣጥተው ስልጠናውን ለወሰዱት 61 የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶችና ተወካዮች ሰርተፊኬት ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

‎‎#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News