አቶ ጳውሎስ በርጋ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

“ከገጠሩ ማህበረሰብ መውሰድ ብቻ ሳይሆን ለገጠሩ ማህበረሰብ መስጠትንም መልመድ መቻል አለብን!”
አቶ ጳውሎስ በርጋ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር
EED: መስከረም 28/2018 ዓ.ም
የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ ዕቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ከገጠሩ ማህበረሰብ መውሰድ እንጂ ወደ ገጠር የሚላክ ነገር እንዳልነበር በማስታወስ አሁን ግን የገጠሩን ማህበረሰብ የመልማት ጥያቄ መመለስ የሚችል የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም ይዘን ቀርበናል ብለዋል።

“እኛ ወይ አባቶቻችን የገጠር ውጤቶች ነን” ያሉት አቶ ጳውሎስ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን በተመቻቸ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ ማህበረሰቦችን የአምራች ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ፕሮግራም በመሆኑ ከገጠሩ ማህበረሰብ መውሰድ ብቻ ሳይሆን ለገጠሩ ማህበረሰብ መስጠትንም መልመድ መቻል እንዳለብን አስረድተዋል።

በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ስናሰብ አርሶ አደሩ የራሱን ማረሻና ሌሎች የግብርና መሣሪያዎችን ጨምሮ ማሻሻልና መቀየር የምንችልበትን አቅም መፍጠር እንደሚጠበቅብን አቶ ጳውሎስ አያይዘው ገልፀዋል።
ሁሉ ነገር በተመቻቸ ሁኔታ እንደማይገጥመን ታሳቢ መደረግ እንደሚገባው የገለፁት አቶ ጳውሎስ ከድህነት ለመውጣት ያለንን ቁርጠኝነት ማሳየት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise