ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

“ከግብርና ስራዎች ባሻገር በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አዳዲስ የሥራ እድሎችን ለገጠሩ ማህበረሰብ መፍጠር ችለናል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED  መስከረም 27/2018 ዓ.ም

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ የ2017 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀምና፣ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ በተመለከተ የክልልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ የአካባቢን ፀጋዎች መሠረት በማድረግ በገጠር አካባቢዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ልማትን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ዶ/ር አለባቸው አያይዘውም ይህ ኢንሺየቲቭ በሀዋሳ 3.2.1 በሚል መርህ ከፀደቀበት ግዜ  ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ፣ በተለይ በ2017 ዓ.ም በገጠር አካባቢዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሠረትን የማስፋፋት ስራ እንደተጀመረ አመላክተዋል።

ለገጠሩ ማህበረሰብ ከግብርና ኢኮኖሚ ውጪ አማራጭ የሥራ እድሎችን በመፍጠር፣ ለብዙ ዜጎች አዲስ የኑሮ ዘይቤን ማስተዋወቅ መቻሉን የገለፁት ዶ/ር አለባቸው ይህ ለውጥ መንግስት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

በልማት መ/ቤቱ  የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ አስተባባሪ የሆኑት  አቶ ፍቃዱ  አክሊሉ  በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 381 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተቋቋመው ለ2,761 ለገጠር አካባቢ ዜጎች አዳዲስ የሥራ እድሎች እንደተፈጠረ ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በገጠር ወረዳዎች 1 ሺህ 713 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ለ33 ሺህ 243 ዜጎች  የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል::

የ2017 ዓ.ም ስኬቶችን መሰረት በማድረግ፣ የ2018 ዓ.ም ዕቅድ የበለጠ ጠንካራ እና ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጎ እንደተዘጋጀ የገለፁት አቶ ፍቃዱ

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ዕቅድ ለማስፈፀም የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን አደረጃጀትን ማጠናከር፣ የጥሬ ዕቃ እና የሰው ሀይል አቅርቦት፣ የፋይናንስ አቅርቦትን ማመቻቸት፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ ማሳደግና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

አቶ ፍቃዱ አክለውም ይህ ኢንሺየቲቭ የገጠር ኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመቀየር ያለመ ብቻ ሳይሆን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን በኢንዱስትሪ ዘርፍ በማስተባበር የተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲኖራቸው ያጠናክራል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ይህ ኢንሺየቲቭ ኢትዮጵያን ወደ ተነቃቃ ኢኮኖሚ ለመውሰድ ትልቅ እድል ስላለው በተከታታይ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለዋል።

ክልሎች በኢኒሺየቲቩ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቷል። 

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት 

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenter

News