ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

“ዜጎች በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ እንዲሰማሩ በማድረግ የገቢ ምንጫቸው እንዲያድግ ማገዝ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው!”

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አመራር፣  ባለድርሻ አካላትና ባለሀብቶች በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪ ልማት ዙሪያ በአርባ ምንጭ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ሀገራችን ካለት የተፈጥሮ ሀብትና እያሻቀበ ካለው ሰፊ የስራ አጥ ቁጥር መጠን አንፃር የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለገጠሩ ማህበረሰብ ለዘመናት ሲሰራው ከነበረው የእርሻ ስራ በተጨማሪ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሲመጣ የሚፈጠረውን አዲስ የአኗኗር  ዘይቤ ታላሚ ያደረገ ኢንሺየቲቭ መዘጋጀቱን ተናግረዋል::

አቶ አብዱልፈታ አያይዘውም ዜጎች መንግስት በንግድ ስርዓቱ ላይ ጣልቃ በመግባት የምርት ዋጋን እንዲያስቀንስ ከመጠበቅ ይልቅ በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የዜጎችን የገቢ ምንጭ ማሳደግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው የአለም አቀፍ ተሞክሮን በማጣቀስ አመላክተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

News