
የማብቃት ፕሮግራም ተሳታፊዎች የምክክር መድረክ በድሬዳዋ ተካሄደ
EED ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (ድሬዳዋ)
አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ማዕከል በማድረግ ለወጣቶች በተለይም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተተገበረ የሚገኘው የማብቃት ፕሮግራም የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በድሬዳዋ ተካሄደ::

የምክክር መድረኩን የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ እንደተናገሩት ድሬዳዋን ከሀገራችንም አልፎ የምስራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ እንደሆነና በተለይም በኢትዮጵያ ታምርት ኢንሺየቲቭ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየሰሩና ለውጥ እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በመድረኩ እንደተናገሩት የማብቃት ፕሮግራም 6,355 አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ በማድረግ ለ241,696 ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠርን ዒላማ አድርጎ የተነሳ ፕሮግራም ነው፡፡
ፕሮግራሙ በአምስት የማኑፋክቸሪንግ ንዑስ ዘርፎች እየሰሩ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር እና በማስፋፋት የሚከናወን ሆኖ በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም ዘርፍ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን የማቋቋም ተግባርን አካትቶ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

የምክክር መድረኩ ፕሮግራሙ ይዞ የተነሳውን ዓላማ ውጤታማ በሆነ አግባብ ለማሳካት የሚያስችልና የኢንተርፕራይዞችን ዕድገትና የወጣትና ሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ዉጤታማ የድጋፍ እና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማሻሻል የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት የወጣቶችን እምቅ አቅም በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ወደ ስራ በማስገባት ለአገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚጠበቅባቸው ሚና እንዲወጡ ማገዝ እንደሚቻል የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ባለድርሻ አካላት ፕሮግራሙን በባለቤትነት መንፈስ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የማብቃት ፕሮግራም ፔትኮ ኢትዮጵያ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፤ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ካዌ በጋራ በመሆን እየተተገበረ ያለና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን፣ ለወጣቶች በተለይም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተተገበረ ነው፡፡

በምክክር መድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ የፔትኮ ኢትዮጵያና ካዌ የስራ ኃላፊዎች፣ፕሮግራሙ ከሚተገበርባቸው ክልሎች፣ ዞኖችና ከተሞች የመጡ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com