ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

“የማያመርት ሀገር የህልውናው ጉዳይ አጠራጣሪ ነው!”

አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED መጋቢት 5/2018 ዓ.ም (አዳማ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ማኑፋክቸሪንግ  ዘርፉን ለመደገፍ በተዘጋጅ ስትራቴጂዎች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ስርዓቶች ላይ ለአመራሮችና ባለሙያዎች  መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።

የተቋሙ ም/ዋና አቶ ጳውሎስ በርጋ በስልጠናው ማጠቃለያ እንደተናገሩት ማኑፋክቸሪንግ የሀገር የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ተወዳዳሪ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ይገባል::

የማያመርት ሀገር የህልውናው ጉዳይ አጠራጣሪ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ይህን በመረዳት ዘርፉን ለመደገፍ የተዘጋጁ ስትራቴጅዎች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ስርዓቶችን በሚገባ በመረዳት ወደውጤት ለመቀየር በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

አቶ ጳውሎስ አክለውም አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ  እንዲሆኑና ችግሮቻቸው በተገቢው ሁኔታ ተፈቷላቸው ወጪና ተኪ ምርት ላይ እንዲሳተፉና ውጤታማ እንዲሆኑ መስራት ይጠይቃል ብለዋል::

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ዘርፉን በእውቀት ለመምራትና ለመደገፍ የሚያስችል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል::

ስልጠናው የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለሚደግፉና ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ 121 ለሚሆኑ አመራርና ባለሙያዎች ላለፉት አራት ቀናት የተሰጠ ሲሆን ዘርፉን ለመደገፍ የተዘጋጁ 8 የሚሆኑ ስትራቴጂዎች፣ መመሪያዎችና የአሠራር ሥርዓቶች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡:

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ፡-

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News