ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

  • የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት እቅድን በተመለከተ ከተቋሙ ስራ አመራር አባላትና ሌሎች መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

‎EED ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉን የ2018 በጀት ዓመት እቅድን በተመለከተ ከስራ አመራር አባላትና ሌሎች መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷበታል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጳውሎስ በርጋ በመድረኩ እንደገለጹት አምራች ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በትኩረት መስራት ይጠይቃል፡፡

የዘርፉን እቅድ በተመለከተ ከክልል አስፈጻሚ ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደተካሄደና መግባባት እንደተደረሰ የጠቆሙት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ይህም ዘርፉን በውጤታማት ለመምራትና ለመፈጸም እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

የዘርፉን እቅድ በአግባቡ ማቀድ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ ጳውሎስ የምንችለውን ብቻ እየሰራን የሀገራችንን እድገት ማምጣት አንችልም፤ “የማንችለውንም” መሞከርና መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል::

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከተኪ ምርት፣ ከማምረት አቅም አጠቃቀምና ከሰው ሐይል ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች  ጋር በተገናኘ አስተያየትና ጥያቄ አቅርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com እናመሰግናለን::

News