ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ  አብዱልፈታ የሱፍ፣  ‎የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED ( ሰኔ 21/2017 ዓ.ም) አዳማ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለተቋሙ መካከለኛ አመራሮች፣ ለዴስክ ሃላፊዎች፣ ለቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች አቅምን ማጠናከር በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የአምራች ኢንተርፕራይዞችን አቅም በማጠናከር  የዘርፉን የወጪ ምርት አፈፃፀም ማሳደግና ተኪ ምርትን በማስፋት የውጭ ምንዛሬን ማዳን አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጃው ያለው ሰራተኛ የተቀራረበና የተሻለ እውቀት ይዞ መደገፍ ይኖርበታል ብለዋል።

የዘርፉን ልማት በዕውቀት ለመደገፍና የተቋሙን እቅድ በተሻለ ለመፈፀም በሚያስችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እንዲያገኙ ስልጠናው መመቻቸቱን የገለፁት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ተገቢውን እውቀት መጨበጥ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የፕሮጀክት እቅድ ትግበራ፣ ክትትልና ግምገማ፣ ስትራቴጂካዊ እቅድና ክትትል፣ የወጪና ተኪ ምርት ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የኢንትራኔት አጠቃቀም በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ይሰጣል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com እናመሰግናለን::

News