ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ ‎የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ተግዳሮቶችን በአሰራር  ስርዓት መፍታት ይገባል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ ‎የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም (ቢሾፍቱ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአምራች ኢንተርፕይዞች የማምረቻና የመሸጫ ቦታ አቅርቦት ዙርያ በተዘጋጀው ጥናት ላይ ከዘርፉ የክልል ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ::

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ  በመድረኩ ባደረጉት ንግግር የአምራች ‎የኢንተርፕራይዝ ልማት ተገቢውን ድጋፍ አግኝቶ ውጤት እንዲያመጣ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችሉ  አሰራሮችን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉን ተግዳሮት ለመፍታት በተሰራው ስራ ዘርፉን ሊደግፉ የሚችሉ በርካታ  የአሰራር ስርዓቶች ተዘጋጅተው  ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጋቸውንም ተናግረዋል።

ለዘርፉ ልማት ዋነኛ ተግዳሮት የሆነው የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግርን በዘላቂነትና ወጥነት ባለው  መንገድ መፍታት የሚያስችል ጥናት መጠናቱን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ጥናቱ ወደ ትግበራ  እንዲገባ በክልል ሃላፊዎችና በባለድርሻ አካላት እንዲገመገም መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ጥናቱ  በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ በሰላም የልማት አማካሪ ድርጅት አማካኝነት ከአምስት ከተሞች ላይ ናሙና በመውሰድ የተዘጋጀ ነው።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

‎ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News