ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረቻና መሸጫ ቦታ አቅርቦትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የተጠናው ጥናት ተገመገመ

EED (ሐምሌ 06/2017 ዓ.ም) ቢሾፍቱ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በአምራች ኢንተርፕይዞችን የማምረቻና መሸጫ ቦታ ላይ የሚታየውን ተግዳሮት በዘላቂነት ለመፍታት ያስጠናውን ጥናት ከዘርፉ የክልል ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የገመገመ ሲሆን የማምረቻና መሸጫ ቦታ አቅርቦትና አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በጥናት መለየቱ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሷል።

መሰረተ ልማት የተሟላለት የክላስተር ልማትና አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ የዘርፉን ልማት ተወዳዳሪነት ማሳደግ እንደሚገባ በመጠቆም በዚህ ላይ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል።

የዘርፉ ልማት ውጤታማ እንዲሆን አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የማምረቻና መሸጫ ክላስተሮች መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸውና ተገቢውን ድጋፍ መስጠት እንዲችሉ እንዲሁም የግሉን ባለሃብት በማሳተፍ  አዳዲስና ሞዴል ክላስተሮች እንዲገነቡ የዘርፉ አመራር በትኩረት መስራት እንዳለበትም በመድረኩ ተመላክቷል።

የክላስተር ልማት ከፍተኛ ካፒታል የሚፈልግ በመሆኑ  ሞዴል ክላስተር በመገንባትና በማልማት  ላይ መንግስትና የግሉ ዘርፍ በጋራ የሚሰሩበትን ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት በጥናቱ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል።

ሞዴል ክላስተር በመገንባትና በማልማት የኢንተርፕራይዞችን የማምረቻና መሸጫ ቦታ ችግር መፍታት ተገቢ ቢሆንም የኢንተርፕራይዞችን ደረጃ ታሳቢ ያደረገና  ደረጃ በደረጃ  የሚገነባበት አማራጭ  የሚቻልበትን ሁኔታ በጥናቱ መታየት እንዳለበት ሃሳብ ቀርቧል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

‎ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News