ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ክቡር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የስራ ዘመን ተጠናቀቀ።

“የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በቀጣይ በሞዴልነት የምናሰፋው ፕሮጀክት ነው!”

ክቡር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የስራ ዘመን ተጠናቀቀ።

EED ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም

ላለፉት 8 ዓመት የቆየው በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የስራ ግዜ ተጠናቀቀ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል በፕሮጀክቱ መዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ፤ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ጥሬ ዕቃ ላይ ዕሴት በመጨመር አምራች ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች የማምረቻ ማሽን ኪራይ ፤ የስራ ማስኬጃ ብድር እንዲሁም የንግድ ልማት ስልጠና በመስጠት ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል::

የቀረበውም ብድር በመደበኛ የብድር ስርዓት ካለው የብድር አመላለስ ምጣኔ በተሻለ ሁኔታ እንዲመለስ በማድረግ ውጤታማ ስራ በማስመዝገቡ ፕሮጀክቱ  በቀጣይ በሞዴልነት እንደሚሰፋ  ሚንስትሩ አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱ በክልሎች መካከል ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር በማድረግ በኢንዱስትሪ ወደኋላ የቀሩ ክልሎችንም ማነቃቃት የቻለ እንደነበር ገልፀዋል::

የፕሮጀክቱ የስራ ግዜ ስለተጠናቀቀ ብቻ የሚተው ሳይሆን የፕሮጀክቱን ሞዴል በማሳደግና በማስፋት ለቀጣይ ምዕራፍ ስራዎቻችንን በስኬት ለመወጣት እንጠቀምበታለን ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በባለሙያ የተደገፈ ትክክለኛ ማሽንና ስልጠና ማቅረብ ከተቻለ ኢትዮጵያውያን ማምረት እንደምንችል በተግባር አረጋግጧል ያሉት አቶ መላኩ ፕሮጀክቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

‎#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

‎ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise #ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News