ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተካሄደው የ2017 ዓ.ም አመታዊ ምዘና የ1ኛ ደረጃን አግኝቷል

EED ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተካሄደው የ2017 ዓ.ም አመታዊ ምዘና ከተጠሪ ተቋማት የ1ኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባደረገው ምዘና በስራ አፈፃፀም፣ በአሰራር ስርዓት፣ እና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ልማት መ/ቤቱ ባስመዘገበው ጥቅል ውጤት የ1ኛ ደረጃን በማግኘቱ የሜዳሊያ፣ የዋንጫ፣ የሰርተፊኬት እና የላፕቶፕ ተሸላሚ ሆኖል።

የልማት መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በሽልማቱ ወቅት እንደተናገሩት ይህ ውጤት በሁሉም አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም በጠንካራ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቅንጅት የመጣ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

እውቅናና ሽልማቱ ለቀጣይ ስንቅ እንደሚሆን የገለጹት ዋና ዳሬክተሩ በቀጣይ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉን በውጤታማነት በመደገፍ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልእኮ በአግባቡ እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News