
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በሀገራዊ የ2018 የልማት እቅድ ላይ ተወያዩ
EED ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በሀገራዊ የ2018 የልማት እቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል::

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት በሀገራችን የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዓለም አቀፍ ተፅዕኖውን መቋቋም የሚያስችሉ እንዲሆኑ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ሳይንጠባጠቡ መፈፀም ይገባል ብለዋል።
እንደተቋም የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፉ ተገቢውን ድጋፍ አግኝቶ ውጤታማ እንዲሆን በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በተሻለ አቅምና አሰራር መፈፀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የ2018 ሀገራዊ የልማት እቅድ በተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የቀረበ ሲሆን የወጪና ገቢ ምርቶች በዓለም ገበያ የሚፈጥሩት ዕድልና ተፅዕኖ ምን ይመስላል በዚህ ላይ በሀገራችን ሀገራዊ ኢኮኖሚን ለማሻሻል ምን ተከናወነ? በቀጣይ በጀት ዓመት የልማት ስራዎችን ለማከናወን ምን ታቅዷል የሚሉ ነጥቦች በሰነዱ ተመላክተው ግንዛቤ ተወስዶባቸዋል።

ለሀገራዊ ኢኮኖሚው እድገት ውጤት የሚያመጡ የልማት ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ በሰነዱ የተገለፀ ሲሆን በዚህም አዳዲስ ምርቶችን ወደ ኤክስፖርት ማስገባትና የኤክስፖርት መዳረሻዎችን ማስፋፋት፣ ሀገራዊ ሰላምን በማረጋገጥ ኢንቨስትመንትን መሳብና የቱሪዝም ዘርፋን ማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና በዲጅታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ፣ ገቢን ማሳደግ ፣ ሁለተናዊ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ማልማትና የስራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግ እንዲቻል በትኩረት መፈፀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፋ እንዲያድግ አዳዲስ ምርቶችን ወደ ኤክስፖርት ማስገባትና የኤክስፖርት መዳረሻዎችን ማስፋት፣ የፋይናንስና የግብዓት አቅርቦቶች እንዲሻሻሉ መስራት፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግና ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቅሷል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2018 እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ተጨማሪ መረጃ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment