ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመርራና ሰራተኞች “ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጅካዊ ቁመና” በሚል ርዕስ ውይይት አካሄዱ

‎EED ጥቅምት 7/2018 ዓ.ም

‎የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመርራና ሰራተኞች “ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጅካዊ ቁመና” በሚል ርዕስ በቀረበ ሰነድ ላይ ወይይት አካሄዱ::

‎የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በውይይት መድረኩ እንደገለፁት ሀገራችን እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና የጠንካራ ህዝብ ባለቤት ብትሆንም በሚገጥሟት የውጭና የውስጥ ፈተናዎች በሚፈለገው ልክ ማደግ አለመቻሏን ጠቅሰው፤ ከዚህ ችግር ለመውጣት በተለይም ጂኦስትራቴጅካዊ ጥቅሞቿን ማስጠበቅ እንድትችል ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል።

‎‎ሰነዱን ያቀረቡት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በገለፃቸው ያለንበት ዓለም ጂኦስትራቴጅካዊ ፉክክር ላይ በመሆኑ  የምናደርጋቸው ማነኛውም ስምምነቶች የሀገርን ህልውና ደህንነትና ሉዓላዊነትና ብልፅግናን የሚያረጋግጡ መሆን ይገባቸዋል።

‎አቶ አብዱልፈታ አክለውም ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ከምንም በላይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

በውይይቱም ሀገራችን ዜጎቿን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ ያላት ቢሆንም የጥቅም ተጋሪ በሆኑ ተፃራሪ አካላት ሃብቷን በሚፈለገው ልክ መጠቀም እንዳልቻለች ተብራርቷል፡፡

ሀገራችን ካላት ጂኦስትራቴጅካዊ ቦታና ከነበራት ቀደምት የሀገረ መንግስት ግንባታ ማግኘት የነበረባትን ሁለንተናዊ  ጥቅም  በውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ምክንያት እያጣች በመሆኑ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር በታደሰ ቁመና ችግሮችን ማለፍና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

እንደተቋም የተያዙ ግቦችን በውጤታማነት በመፈፀም የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን ድርሻ ከፍ ማድረግ እንዲቻል በዘርፉ ያለው አመራርና ባለሙያ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት በውይይቱ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት 

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News