
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ
EED ህዳር 18/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ፡፡

የስምምነት ፊርማውን ያካሄዱት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ ናቸው፡፡
የስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ተቋማት ያካበቷቸውን የቴክኖሎጂ አቅሞችን እና ልምዶች በማቀናጀት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በቴክኖሎጂና የመለዋወጫ አቅርቦት፣ በፈጠራ ስራና ፐሮቶታይፕ ግንባታ፣ በማሽን ምርትና ኮሚሽኒንግ ጋር በተያያዘ በጋራ ለመስራትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ነው፡፡
የልማት መ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደተናገሩት ኢትዮ-ኢንጂነሩንግ ግሩፕ ትልቅ አቅም ያለው ተቋም በመሆኑ በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚስተዋለውን የማምረት አቅም አጠቃቀም ክፍተት ለመሙላትና አቅማቸውን ለማሳደግ እንዲሁም በመለዋወጫ ምክንያት ስራ ያቆሙ ኢንተርፕራይዞችን ወደስራ ለማስገባት ስምምነቱ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ስምምነቱ የባለሙያዎችንም አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ወደተግባር እንዲገባም መረባረብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ በበኩላቸው ተቋሙ የተቋቋመው በዘርፉ አቅም ለመፍጠር በመሆኑ ያላቸውን ተሞክሮና ቴክኖሎጂ በመጠቀም የኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ ወደስራ እንዲገባና ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህንን ስራ የሚከታተል አደረጃጀት መፈጠሩንም አስታውቀዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
#የኢትዮጵያ_ኢንተርፕራይዝ_ልማት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ቲክ_ቶክ: https://www.tiktok.com/@et.enterprisedevelopment
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise