
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ ስምምነት አደረጉ
EED ግንቦት 12/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ፊርማ አከናውነዋል፡፡
የፊርማ ስነ ስርዓቱን ያከናወኑት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጥላሁን ብርሃኑ ናቸው፡፡

የጋራ ስምምነቱ ዓላማ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባር ተኮር ስልጠናዎች፣ የፋይናንስ፣ የግብዓት አቅርቦትና ሌሎች ድጋፎችን መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በቅንጅት ለመስራት ነው፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
#ስለኢትዮጵያ_ኢንተርፕራይዝ_ልማት ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com እናመሰግናለን፡፡