
ኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት ዓመቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከአመራሩና ሰራተኞች ጋር ገመገመ
EED ሰኔ 28/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ጋር ገምግሟል::

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ተቋሙ አምራች አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ በመደገፍ ቁጥራቸው እንዲጨምር እንዲሁም አቅማቸው እንዲጠናከሩና ተወዳዳሪ ምርት እንዲያመርቱ ለማድረግ በበጀት ዓመቱ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ ስራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ መፈፀም ላይ መሻሻሎች የታዩ ቢሆንም በቀጣይ በጀት ዓመት በወቅቱ ስራዎችን ማከናወን እንዲቻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በ2017 በአፈፃፀም የነበሩ ክፍተቶችን በማረም ጠንካራ አፈፃፀሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመድረኩ የተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com