
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ
EED ጥር 15/2018 ዓ.ም ( አርባ ምንጭ)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከክልል የዘርፍ አስፈጻሚዎች ጋር ሲያካሂደው የነበረውን የ2018 በጀት አመት 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አጠናቀቀ::

በመድረኩ ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት የገበያና የግብአት ትስስር ችግሮችን ለመፍታት የለሙ የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርሞችን ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እንዲጠቀሙ ማበረታታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሀገራችን ገጠራማ አካባቢዎች ከግብርና ኢኮኖሚ በተጨማሪ አዲስ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩ ባሻገር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎችን በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሺየቲቭ አማካኝነት ማስተዋወቅ እንደሚገባ ያመላከቱት አቶ አብዱልፈታ ዕቅዶች ሲከለሱም ያደጉ ሀገራት የደረሱበትን ደረጃ ለመድረስ “በመፍጠር፣ በመፍጠንና አንዳንድ ጊዜ በመዝለል” ወደ ብልፅግና የሚያደርሱ ተግባራትን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረው፣ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት እንደሚሰሩ ገልፀዋል::

የኢትዮጽያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአቅም ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል::

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቷል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!